ታላቅ ደስታ የምስራች

25 የገና በዓል የፅሞና ንባቦች በጆን ፓይፐር

ኢየሱስ ለገና የሚፈልገው ምንድን ነው?

በዓለም ዙሪያ ያሉ ክርስቲያኖች የገና በዓልን ለማክበር ሲዘጋጁ ልባቸው ልዩ በሆነ ደስታ እና ናፍቆት በተሞላ ግምት ይሞላል፡፡ ታላቅ ደስታ የምስራች በተሰኘው መፅሐፍ ውስጥ ጆን ፓይፐር በዚህ የልደት በዓል ወቅት አንባቢዎቹ ልባቸውን ወደ ኢየሱስ እንዲያዞሩ ይጋብዛል፡፡

ታላቅ ደስታ የምስራች የተሰኘው መፅሐፍ የገናን ክብር በአዲስ መልክ በፊታችን ያቀርብልናል፡፡ ለማንበብ ጊዜ ለሌላቸው ሰዎች ምነኛ ግልግል ነው … እያንዳንዱን ቀን ስለ ጌታችን ኢየሱስ እያሰቡ ማረፍ፣ መደሰት፣ እና መነቃቃት የሚችሉበት! (ሬይ ኦርትለንድ)

በኢየሱስ እውነት የተሞላ የከበረ ሃብት ሳጥን

ይህ መፅሐፍ በውስጡ 25 ዕለታዊ ንባቦች ያሉት ሲሆን እያንዳንዳቸው አንድ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ ያተኮረ አጭር ዕይታ ይዘዋል፡፡ ለግል ጥናት እና ለቤተሰብ የፅሞና ጊዜ እጅግ ተስማሚ የሆኑና በኢየሱስ ክርስቶስ ውልደት አማካኝነት የተገኘውን የደህንነት ቃልኪዳን ታላቅነት ለማብሰልሰል የሚረዱ ማጥኛዎች ናቸው፡፡

የገና በዓል ደስታን ለሌሎች ያጋሩ

© 2021 ወንጌሉ፤ አ.አ፣ ኢትዮጵያ